አቡጊዳ – ግንቦት 17 ቀን 2002
በአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳይ ሃላፊ ሚስተር ጆኒ ካርሰን ዛሬ በሰጡት አስተያየት፣ ምርጫዉ የአለም አቀፍን መስፈርት ያልጠበቀ እንደሆነ ገለጹ። «የኢትዮጵያ መንግስት ላለፉት አሥራ ስምንት ወራት የተሰጠዉን ድምጽ ሁሉ ለመዉሰድ ግልጽ የሆኑ እርምጃዎች ሲወስድ ነበር» ያሉት ጆኒ ካርሰን፣ ምርጫ በሚደረግበት ጊዜ ምርጫዉ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ህዝቡን ያለ ስጋትና ያለ ፍርሃት እንዲመርጥ የሚያስችለዉ የዴሞክራሲ ተቋማትን ኢትዮጵያ መገንባት እንዳለባት አስረድተዋል።
ጆኒ ካርሰን ምርጫዉን አሜሪካ ትቀበለዉ አትቀበለዉ ለመግለጽ ፈቃደኛ አልሆኑም። ሁኔታዉን እንደሚከታተሉ የገለጹት ጆኒ ካርሰን «የምርጫዉ ሁኔታ በሃዘን ነዉ የተቀበልነዉ» ሲሉም የተሰማቸዉን ቅሬታ በመግልጽ አጠናቀዋል።
እንደሚታወቀዉ ከአሥራ ስምንት ወራት በፊት ምርጫዉን ለማሸነፍ በጀመሩት እንቅስቃሴ ምክንያት ከአሥራ ስምንት ወራት በፊት ወ/ት ብርትካን ሚደቅሳ በግፍና በጭካኔ መታሰሯ ይታወቃል። ጆኒ ካርሰን «አሥራ ስምንት ወራት» ሲሉ ይችኑ ታላቅ የዴሞክራሲ ሴት አስበዉን እንደሆነም ግልጽ ነዉ።
የአዉሮፓ ሕብረትም የምርጫዉን ፍትሃዊን ዴሞክራሲያዊ አለመሆን ሲያብራራ ከጠቀሳቸዉ ምክንያቶች አንዱ የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ መታሰር ነዉ።
በተያያዘ ዜና የሕወሃት/ኢሓዴ ደጋፊዎች ከሚያደርጉት ዳንኪራና ሰልፎች በስተቀር ህዝቡ በጸጥታ ዉስጥ ነዉ የሚገኘዉ። የፌደራል ፖሊስና የደህንነት አባላት ጦር ሜዳ ያሉ ይመስል በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ ይገኛሉ።


Leave a Reply