ከ536 መቀመጫዎች የአቶ መለስ ቡድን 534 ቱን አሸነፈ ተባለ
አቡጊዳ – ግንቦት 17 ቀን 2002
ምርጫ ቦርድ ባወጣዉ ዘገባ፣ አራቱ በኢሕአዴግ ዉስጥ ያሉ ግንባሮች እንዲሁም በአፋር በሶማሌ በጋምቤላ በሃረሬ ..ያሉ የገዢዉ ፓርቲ ተቀጥያዎች፣ ይፋ ከተደረጉት ከ 536 መቀመጫዎች 534 ቱን ማሸነፋቸዉን ምርጫ ቦርድ አሳወቀ። ከ536 ቱ ዶር አሸብር የሚባሉ አንድ የግል ተወዳዳሪ በደቡብ ክልል፣ አንድ የመድረኩ ተወዳዳሪ ደግሞ በአዲስ አበባ አሸናፊ ተብለዋል። የስነ ምግባር ደንቡን የፈረሙና በወቅቱ ለገዢዉ ፓርቲ መጠነኛ አለም አቀፍ ድጋፍ ያስገኙለት መኢአድ፣ ኢዴፓና የአየለ ጫሚሶ ቡድን፣ ኢሕአዴግ ከዘረፈዉ ትንሽ ያቀምሳቸዋል ተብሎ ቢጠበቅም፣ በዜሮ ተመልሰዋል። በሶማሌ ክልል 2፣ በጋምቤላ 1፣ በቤኔሻንጉል 7 ፣ በአማራዉ ክልል 1 ፣ በአጠቃላይ በ 11 መቀመጫዎች ገና ይፋ ያልተደረጉ ቢሆኑም፣ እነዚህም ገዢዉ ፓርቲ እንደሚወስዳቸዉ ብዙዎች ይገምታሉ። በዚህ ምክንያት በሚቀጥለዉ ፓርላማ ተቃዋሚዎች 2 ብቻ በመሆናቸዉ አስተያየት ለመስጠት ሰፊ ጊዜ ይኖራቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።


Buy:Lasix.Cozaar.Zocor.Nymphomax.Prozac.Buspar.Aricept.Lipitor.Seroquel.Ventolin.Female Cialis.Acomplia.Female Pink Viagra.Advair.Lipothin.Benicar.SleepWell.Wellbutrin SR.Amoxicillin.Zetia….